ይህ መጸሃፍ ከትውልድ ወደ ትውልድ መተላለፍ ያለበት ቅርስ ነው ፡፡ ደራሲው ሀዲስ አለማየሁና ተራኪው ወጋየሁ ንጋቱ ምስጋናየ ወደር የለውም ። ስራቸ ውን ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለዓለም ስላካፈሉን እናመሰግናለን። እንደነዚህ የተከበሩ ደራሲና ተራኪ በግሌ ወደፊት ይገጥሙኛል ብዬ አላምንም ። ይህ መጽሃፍ አስተማሪ ነው ፤ ተደጋግሞ ቢሰማም የሚሰለች አይደለም :: አብዛኛው ዜጋዋ ማንበብና መጻፍ በማይችለው በኢትዮጵያ ውስጥ በተለይም በኢትዮጵያ ራዲዮ የእሑድ ምሽት “ከመጻሕፍት ዓለም” ተደጋግሞ በመተረኩ ትልቅ ዕውቅናን በሚያነበውም በማያነበውም ዘንድ ያተረፈ ነው። በተጨማሪ ፤ ፍቅር እስከመቃብር ትረካ ውስጥ በቴዲ አፍሮ እና እጅጋየሁ ሺባባው የአርት ስራ የታጀበ በመሆኑ ለጥበብ ስራቸው ከልብ እናመሰግናለን። ጥበብ ፤ ሁል ጊዜ በቃላት ሊነገሩ የማይችሉ ነገሮችን መናገር ይችላሉና። በእራሳቸው የእጅ ሙያ አማካኝነት፤ እኛ አንድ ዓይነት ስሜት የሚሰማን እኛ ብቻ አለመሆናችንን ማጽናኛ በመስጠት ስሜታችንን እንዲያንቀሳቅሱ እና እንዲያረጋግጡ ረድተውናልና። ስለዚህ የመጸሃፉን ትረካ እድል ገጥሟችሁ ሳትሰሙት የቀራችህ ወገኖች ካላችሁ ፤ ሙሉውን ትረካ እንድትሰሙት አቅርቤላችኋለሁ ። በተሪኩ እንደምትደሰቱ ተስፋ አደርጋለሁ! ክፍል 2 በሚቀጥለው ሳምንት ይቀጥላል! በ Apple, google, Anchor, Breaker, Spotify, RadioPublic and Pocket Cast ላይ ይጠብቁን!
--- Send in a voice message: https://podcasters.spotify.com/pod/show/bitew-t/message

