Show notes
ከማዕበሉ በፊት ትናንሽ ማዕበሎች (Storms Before the Storm)
ጤና ይስጥልኝ ኣድማጮቼ! እንኳን ወደ ኢትዮባልካን ፖድካስት በሰላም መጣችሁ።
በዛሬው ፕሮግራማችን የዩጎዝላቪያ ፅንፈኛ የብሄር ፖለቲከኞች ስትራተጂና አካሄድ፥ መሰረታዊ ፀባያትና አላማችንን ያሳካልናል ብለው ከተጠቀሟቸው ዘዴዎች መካከል ዋና ዋናዎቹን እንመለከታለን።
ሃሃ፥ Modus operandi ነው ዛሬ baby!
ይሄንንም ከሌሎች ሃገራት ታሪኮች እያጣቀስኩ ለማቅረብ እሞክራለሁ።
ላዛም ነው እነ ሩዋንዳ፥ ናዚ ጀርመኒ ና ሌሎችም መጠቃሳቸው አይቀርም።
የዛሬውን ፕሮግራም በጣም ግልፅ በሆነ ምክንያት እንደምትወዱት እርግጠኛ ንኝ።
በዚህ ፕሮግራም ከተካተቱት ዋና ዋና ጭብጦች ምካከል የሚከተሉት ከነ ምሳሌያቸው ቀርበዋል።
- የተጠቂነት ስሜትንና ጥላቻን ማስፋፋት
- በዩጎዝላቪያ ተቋማቶች ቅቡልነት እንዳይኖራቸውና ስርአት አልበኝነትም እንዲሰፍን ማድረግ
- ከውስጥ የማፅዳት ዘመቻ
- አብዛኛውን ህዝብ የተገዳጅ ደጋፊ ማድረግ ወይም ዝም እንዲል ማስገደድ
- እየተደረጉ ያሉ ወንጀሎችንና የሰብአዊ ቀውሶችን መካድ ወይም አለማመን (creating a scenario of plausible deniability)
- ለአማራጭ ሀሳቦችና ሁሉን አቀፍ ለሆኑ ድርድሮች በርን ዝግ ማድረግ
- የብሔር ቅራኔዎችን ወደ ሃይማኖት ቅራኔነት ወይም ሌላ የቅራኔ መስኮችን ፈልጎ ወደዛ ማስፋት ነው
- እና ሌሎችም
Listen to yourself while listening to this program.
Enjoy.
--- Send in a voice message: https://podcasters.spotify.com/pod/show/ethio-balkan/message
