====== كلمات الحياة" ، "أخبار جيدة" ، "ترانيم الإنجيل" - اللغات الرئيسية المستخدمة في الدولة إذا إريتريا" / "Words of Life", "Good News", "Gospel Songs" - Main Languages Spoken in State if Eritrea======
====== كلمات الحياة" ، "أخبار جيدة" ، "ترانيم الإنجيل" - اللغات الرئيسية المستخدمة في الدولة إذا إريتريا" / "Words of Life", "Good News", "Gospel Songs" - Main Languages Spoken in State if Eritrea======
Eritrea Words of Life
አማርኛ - "ኢየሱስ ስለ እኛ ሞቷል".mp3
2 minutes Posted Dec 15, 2022 at 2:41 am.
0:00
2:12
Download MP3
Show notes
Amharic - "Jesus Died for Us".mp3 /  "الأمهرية - "يسوع مات لأجلنا.mp3 //ዮሐንስ 1ቃል ሥጋ ሆነ1. በመጀመሪያ ቃል ነበረ፤ ቃልም ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ፤ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ። 2. እርሱም በመጀመሪያ ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ። 3. ሁሉ ነገር በእርሱ ተፈጥሮአል፤ ከተፈጠረው ሁሉ ያለ እርሱ የተፈጠረ ምንም የለም። 4. ሕይወት በእርሱ ነበረች፤ ይህች ሕይወት የሰው ብርሃን ነበረች። 5. ብርሃንም በጨለማ ያበራል፤ ጨለማውም አላሸነፈውም።1፥5 ወይም ጨለማው ግን አላወቀውም 6. ከእግዚአብሔር የተላከ ዮሐንስ የተባለ አንድ ሰው ነበረ። 7. ሰዎች ሁሉ በእርሱ በኩል እንዲያምኑ፣ ስለ ብርሃን ምስክር ሆኖ ለመቆም መጣ፤ 8. ስለ ብርሃን ሊመሰክር መጣ እንጂ እርሱ ራሱ ብርሃን አልነበረም። 9. ለሰው ሁሉ ብርሃን ሰጪ የሆነው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም እየመጣ ነበር።1፥9 ወይም ይህ ወደ ዓለም ለሚመጣ ሰው ብርሃን የሚሰጥ እውነተኛው ብርሃን ነበረ 10. እርሱ በዓለም ውስጥ ነበረ፤ ዓለም የተፈጠረው በእርሱ ቢሆንም እንኳ፣ ዓለም አላወቀውም። 11. ወደ ራሱ ወገኖች መጣ፤ የገዛ ወገኖቹ ግን አልተቀበሉትም፤ 12. ለተቀበሉትና በስሙ ላመኑት ሁሉ ግን የእግዚአብሔር ልጆች የመሆን መብት ሰጣቸው። 13እነዚህም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ፣ ከደም1፥13.  ወይም ከሰው ውሳኔ ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም። 14. ቃልም ሥጋ ሆነ፤ በመካከላችንም አደረ፤ እኛም ጸጋንና እውነትን ተሞልቶ ከአባቱ ዘንድ የመጣውን የአንድያ1፥14 ወይም አንድ ልጁ የሆነው ልጅን ክብር አየን። 15. ዮሐንስም፣ “ ‘ከእኔ በኋላ የሚመጣው ከእኔ በፊት ስለ ነበረ ከእኔ ይልቃል’ ብዬ የመሰከርሁለት እርሱ ነው” በማለት ጮኾ ስለ እርሱ መሰከረ። 16. ከእርሱ ሙላት ሁላችንም በጸጋ ላይ ጸጋ ተቀብለናል፤ 17. ሕግ በሙሴ በኩል ተሰጥቶ ነበር፤ ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል መጣ። 18. ከቶውንም እግዚአብሔርን ያየ ማንም የለም፤ ነገር ግን በአብ እቅፍ ያለው አንድያ ልጁ1፥18 አንዳንድ ቅጆች አንድ ልጁ ይላሉ የሆነው አምላክ እርሱ ገለጠው።