
ወንድማማቾቹ ዮሐንስ እና ዮናስ መምህር ፣ ገጣሚ እና አብዮተኞች ነበሩ። በተለያየ ዕርከንም ቢሆን በኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ ውስጥ ተሳትፎ ነበራቸው። ዮናስ የታላቅ ወንድማቸው ዮሐንስ አድማሱን ጅምር ሥራዎች ማጠናቀቅ በሕይወታቸው ትልቅ ትኩረት የሰጧቸው ጉዳዮች እንደነበሩ የቅርብ ወዳጆቻቸው በተደጋጋሚ ይናገራሉ። የታላቅ ወንድማቸው እስኪ ተጠየቁ የተባለ የግጥም መጽሐፍ ለሕትመት ያበቁት ዮናስ ናቸው።
የኃይሌ ገሪማን ጤዛ ፊልም ካፕሽን ከእንግሊዘኛ ወደ አማርኛ በመተርጎም አብረዋቸው የሰሩት ሔራን ሰረቀ ብርሃን እንዲያውም "ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ፤ አጭር የሕይወቱና የጽሑፉ ታሪክ" የተባለውን መጽሐፍ ሲያልቅ የእኔም ጉዞ ያበቃል» ይሉ ንደነበር ለመገናኛ ብዙኃን ተናግረው ነበር።
"ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ፤ አጭር የሕይወቱና የጽሑፉ ታሪክ" ለሕትመት በቅቶ በብሔራዊ ቲያትር የተመረቀ ዕለት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ ዳይሬክተር የነበሩት ፕሮፌሰር ማስረሻ ፈጠነ ያሰሙት ንግግር ዮናስ ምን ያክል ተጨናቂ (meticulous) እንደነበሩ የሚጠቁም ነው። ይኸኛው ደግሞ ሐይማኖት አለሙ ሶስቱ ዮዎች በሚል ርዕስ የዮፍታሔ ንጉሤን፣ የዮሐንስ እና ዮናስ አድማሱን የሕይወት ታሪክ አጠር አድርጎ ያቀረበበት ነው።
አጭር የሕይወት ታሪክ ሐይማኖት ዓለሙ እንደተረከው
Oct 15, 2020
7 min

"ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ፤ አጭር የሕይወቱና የጽሑፉ ታሪክ" የተባለው መጽሐፍ ከሰባት አመታት በፊት በብሔራዊ ቲያትር ሲመረቅ ጸሐፊው ዮሐንስ አድማሱ እና ወንድማቸው እና አሰናኙ ዮናስ አድማሱ (ዶክተር) በሕይወት አልነበሩም። የታሪኩ ባለቤት ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴም ቢሆኑ ሕይወታቸው ካለፈ ረዥም አመታት ተቆጥረዋል።
ዮፍታሔ ንጉሴ አርበኛ ፣ ባለቅኔ እና የቲያትር ባለሙያ ነበሩ። በ1887 ዓ.ም. በጎጃም ደብረ ወርቅ ተወልደው ደብረ ኤልያስ ዜማ እና ቅኔ የተማሩት ዮፍታሔ የአሮጌው ሥርዓት ሰው ቢሆኑም አብዮተኛው እና ኮምዩኒስቱ ዮሐንስ ቀርቦ እንዲያጠናቸው እንዲመረምራቸው የሚያደርግ ተክለ ስብዕና ነበራቸው።
የሕይወት ታሪካቸው እና ሥራዎቻቸው ላይ ያተኮረው ይኸው መጽሐፍ ተጀምሮ ለሕትመት እስኪበቃ ከአራት አስርት አመታት በላይ ወስዷል። ዮሐንስ የጀመረውን ያጠናቀቁት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር የነበሩት ቁጥቡ ዮናስ ናቸው። ዮናስ ዝምተኛ እና ቁጡ መስለው ቢታዩም ስለ ስነጽሁፍ የነበራቸው እውቀት፣ ለግጥም የነበራቸው ቅናት የትንኔዎቻቸው ምጥቀት እና የቋንቋቸው ለዛ ሌላ ነበር። ይኸ የፕሮፌሰር ማስረሻ ፈጠነ ዲስኩር በተለይ ስለ ሕትመት ሒደቱ ብዙ ይናገራል። ሸገር ትሪቢዩን ሊደመጥ የሚገባው ነው ብሎ በማመን አቅርቦታል።
Oct 11, 2020
13 min