====== كلمات الحياة" ، "أخبار جيدة" ، "ترانيم الإنجيل" - اللغات الرئيسية المستخدمة في الدولة إذا إريتريا" / "Words of Life", "Good News", "Gospel Songs" - Main Languages Spoken in State if Eritrea======
====== كلمات الحياة" ، "أخبار جيدة" ، "ترانيم الإنجيل" - اللغات الرئيسية المستخدمة في الدولة إذا إريتريا" / "Words of Life", "Good News", "Gospel Songs" - Main Languages Spoken in State if Eritrea======
Eritrea Words of Life
አማርኛ - "ኢየሱስ፡ መምህር እና ፈዋሽ".3gp
58 minutes Posted Dec 15, 2022 at 2:38 am.
0:00
58:26
Download MP3
Show notes
 Amharic(አማርኛ) - "Jesus: Teacher & Healer“.3gp / 3gp." الأمهرية - "يسوع: المعلم والمعالج //1 ቆሮንቶስ 131. በሰዎችና በመላእክት ልሳን 13፥1 ወይም ቋንቋዎች ብናገር፣ ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚ ጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሿሿ ጸናጽል ነኝ። 2. የትንቢት ስጦታ ቢኖረኝ፣ ምስጢርን ሁሉና ዕውቀትን ሁሉ ባውቅ፣ ተራራንም ከቦታው የሚነቅል እምነት ቢኖረኝ፣ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ። 3. ያለኝን ሁሉ ለድኾች ብሰጥ፣ ሰውነቴንም እንዲቃጠል ለእሳት ብዳርግ፣ 13፥3 አንዳንድ የጥንት ቅጆች፣ እንድታበይ አሳልፌ ብሰጥ ይላሉ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም። 4. ፍቅር ታጋሽ ነው፤ ደግሞም ቸር ነው። ፍቅር አይመቀኝም፤ አይመካም፤ አይታ በይም፤ 5. ተገቢ ያልሆነ ነገር አያደርግም፤ ራስ ወዳድ አይደለም፤ አይበሳጭም፣ በደልን አይቈጥርም። 6. ፍቅር ከእውነት ጋር እንጂ በዐመፅ ደስ አይሰኝም። 7. ፍቅር ሁል ጊዜ ይታገሣል፤ ሁል ጊዜ ያምናል፤ ሁል ጊዜ ተስፋ ያደርጋል፤ ሁል ጊዜ ጸንቶ ይቆማል። 8. ፍቅር ከቶ አይወድቅም፤ ነገር ግን ትንቢት ቢሆን ይሻራል፤ ልሳንም ቢሆን ይቀራል፤ ዕውቀትም ቢሆን ይሻራል። 9. ምክንያቱም የምናውቀው በከፊል ነው፤ ትንቢት የምን ናገረውም በከፊል ነው። 10. ነገር ግን ፍጹም የሆነው ሲመጣ በከፊል የነበረው ይሻራል። 11. ልጅ ሳለሁ እንደ ልጅ እናገር ነበር፤ እንደ ልጅ ዐስብ ነበር፤ እንደ ልጅም አሰላ ነበር። ከጐለመስሁ በኋላ ግን የልጅነትን ነገር እርግፍ አድርጌ ትቻለሁ። 12. አሁን የምናየው በመስተዋት ውስጥ እንደሚታይ በድንግዝግዝ ነው፤ በዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን። አሁን የማውቀው በከፊል ነው፤ በዚያን ጊዜ እኔ ራሴ ሙሉ በሙሉ የታወቅሁትን ያህል ዐውቃለሁ። 13. እንግዲህ እምነት፣ ተስፋ፣ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ፤ ከእነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው።