====מילות חיים", "חדשות טובות", "שירי הבשורה" - עם שפות עיקריות המדוברות בישראל" / "Words of Life", "Good News", "Gospel Songs" - With Major Languages Spoken in Israel ====
====מילות חיים", "חדשות טובות", "שירי הבשורה" - עם שפות עיקריות המדוברות בישראל" / "Words of Life", "Good News", "Gospel Songs" - With Major Languages Spoken in Israel ====
Israelwordsoflife
שפה אמהרית - "ישו מת בשבילנו".mp3
2 minutes Posted Sep 2, 2022 at 2:00 am.
0:00
2:12
Download MP3
Show notes
አማርኛ ቋንቋ - "ኢየሱስ ሞተልን".mp3 / Amharic Language - "Jesus Died for Us".mp3 //የዮሐንስ ወንጌል - ምዕራፍ 1 1 በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።2 ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ።3 ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።4 በእርሱ ሕይወት ነበረች፥ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች።5 ብርሃንም በጨለማ ይበራል፥ ጨለማም አላሸነፈውም።6 ከእግዚአብሔር የተላከ ስሙ ዮሐንስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤7 ሁሉ በእርሱ በኩል እንዲያምኑ ይህ ስለ ብርሃን ይመሰክር ዘንድ ለምስክር መጣ።8 ስለ ብርሃን ሊመሰክር መጣ እንጂ፥ እርሱ ብርሃን አልነበረም።9 ለሰው ሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም ይመጣ ነበር።10 በዓለም ነበረ፥ ዓለሙም በእርሱ ሆነ፥ ዓለሙም አላወቀውም።11 የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም።12 ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤13 እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም።14 ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን።15 ዮሐንስ ስለ እርሱ መሰከረ እንዲህም ብሎ ጮኸ። ከእኔ በኋላ የሚመጣው እርሱ ከእኔ በፊት ነበረና ከእኔ ይልቅ የከበረ ሆኖአል፤ ስለ እርሱ ያልሁት ይህ ነበረ።16 እኛ ሁላችን ከሙላቱ ተቀብለን በጸጋ ላይ ጸጋ ተሰጥቶናልና ሕግ በሙሴ ተሰጥቶ ነበርና፤17 ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ሆነ።18 መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው።